ቢኒያም እባላለሁ
በዚህ ድህረገጽ
ከአደማመቅሽ : እንጂ : ከአመጣጥሽ : ክፉ : ነበርሽ ፤
አምርሮ : መውደድና : አክርሮ : መጥላት : በአንድ : ልብ : በአንዲት : ቅፅበት : ሲሰርፁ ⁼⁽Emotional ambivalent⁾ ስትሆን : ናላህና : ልብህ : ማያባራ : ጥል ⁼(infinite game) : ይጫወቱ : ይሆናል።
ወደ ቴሌግራም ገፄ ያምሩ
Let's review
[መናገር አቃተኝ
ልሳኔ ተዘጋ]
[የባከነው ቀልቤ
ከአይንሽ እየረጋ]
[ላህያ ወዘና! ]
[እግዚኦ....መነን ቃና]
[የላተና ላቦት
ሳቅሽ ያገነፈው]
[ሀሳቤን ይፋጃል
ልቤን እያላፈው]
Website : www.eftalhomtimes.com
Email : eftalhomt@gmail.com
Phone : +2519 3139 2175
Poems
Biniyam T.
| ሳስባት ተስፋ አልባነቴ ይቸሰችሳል !
" በምን ? " በሚከነብል እንባዋ ይሆን ? ፤ ' ሰቀቀኔ ' እንዳያጬሳት እፈራለሁ። አውቃለሁ ከእለታት በአንዱ ቀን ከአለም ቁምፈ ፍርግሜን ወስዳ ⁵እጅብተ በረሂ አውርሳኝ ልትወልደኝ ትዳክር እንደነበር ! " የማይወለድ ሽል እንዴት አልታከተሽ ? " መጠየቅ ያምረኛል ፤ ቆፈኔን የት ዘለቅሁ ? [ እሷነቷ ] መቅደስ ነው ፤ ከሚጤስ ሉባንጃ ሙቀትን ከመዓዛ የሚቸር ። የዜማዋ ዝማሜ ዘለዓለሜን የሚተርክ ! [ እናት ናት 💚 ] ቁንጅናዋን ረስታ ለነፍሴ ልትለምን የመነነች እማምኔት ! የገዳሟን ወርድና ቁመት ላሰላ እጥራለሁ ፤ አለም ናት ፤ " ግዝፈቷ " አይገባኝም ! የእውነቷ ከእውቀቴ መራቅ ፤ ⁶የፈንታስዬ አውታር ባገመደቻቸው እውነትና እምነት በሀሳቤ ልክ እንደማትሰላ ያወሰኛል ! ___ ⁵ እጀብተ በረሂ = the cluster of genes ⁶ የፈንታስዬ = my fantasy
Biniyam T.
Why am I here?
አንጋጠጥሁ ፤ ከሰማዪ ወለል የተሰደሩ ከዋክብት እያጤንሁ ስለነባረዊነቴ እጠይቃለሁ! - ኑረቴ ያፀይፈኛል:: ስለምን ⁴ሁለንተናን እንድሻማ ስጋ ለበስኩ ? ጠ የ ቅ ሁ ት! ስለምን ዝም ትለኛለህ? ⁵አላዊ ንሞናህን ስጠኝ እንጂ! - ስለምን ያላለቀ ንድፍ ወደ ምድር ትሰደዳለህ? - ⁶በጅምር የቀሩ ግለ ባህሪያትን መጨረስ ስለምን አቃተህ? “paradox of the stone” እንደ አዲስ አቃጨለብኝ! “Either God can create the stone which He cannot lift, or He cannot create a stone which He cannot lift. “ The Reality Is Questionable! ስለ አመክንዮው መደምደም ቢያስፈራኝም ፤ የአመክንዮውን ተምሳሌታዊ ዝምድና ለመስጠት ደፈርኩ! _____ ⁴the universe ⁵your purposive sample ⁶why do u fail to complete personalities Inspired by ፦ የአያ ሙሌ "እውነት ከመንበርህ የለህማ! " girl, u're the relief of this 💚
Biniyam T.
ከእግዜር ምሉዕ ቁጥር ከሰባተኛው ወር ከሰባተኛው ቀን....
ከእግዜር ምሉዕ ቁጥር ከሰባተኛው ወር ከሰባተኛው ቀን.... ከተማሪ ቤት ስንለቀቅ ሀሩር ያደባየው አካሌ ዝሎ እረፍቱን ያስሳት ዘንድ እየተጣደፈ ተመውደቂያው ሊደርስ ይዳክራል። [ድካም : እና : የማረፍ : ተስፋ : መኻል : ርግበቷን : ያከረረችበት : የጥድፈት : ክር] የእርምጃ ታዛዎቼ ርቀትን እያጣፉ የእረፍቴን ካስማ በጥረታቸው ያምጡ ዘንድ በርትተዋል። የቤቴን በር ያስገባኝ ያህል ከፍቼ መልሼ ገረበብኩት...መምጣቴ ይታወቅልኝ ዘንድ አደርገው እንደነበር ድምፀቴን ሰቅዤ አያቴን ተጣራኃት ካለወትሯዋ "ናማ" የሚል እንስፍስፍ መልሷን አጣሁ ዝም! [የልብህ : ሚዛን : ያልደፋላቸው : ዝም : ሲሉህ 'እረፍትህ' ነው።... ለምትሳሳላቸው : ግን : ድምፆቻቸው : የልብህ : ምት : ደርዞች : ናቸው : ዝምታቸው : ይረብሽሃል] ፈጥኜ ከቤት ገባሁ....የአያቴ አይኖች እምባ አቅርረዋል [ትኩስ : ስሜት : ልፈነግላቸው : የሚታገለውን : እምባ] ተጠረጴዛው አንፃር ሁለት የአክስቴ ልጆች አይናቸውን ከአይኔ እያንከባለሉ ቁመዋል..ተእይታቸው ስር ለሴኮንዶች ሲያከርሙኝ..የመበርበር ስሜት እየተሰማኝ እኔነቴን አጣሁ! ከመሃላቸው አንደኛው 'ናማ የምንሄድበት ቦታ አለ' 'እምቢየው እረፍት ነው ሚሻው'መለስኩ 'ግድ የለህም ትመለስ እና ታርፋለህ' አለኝ ልምምጥ በበዘው ድምፀት [በእግር : አዘገምን : ሴይቼንቶ : ተሳፈርን : ታኪሲ : ተኮናተርን : ግራ : እየገባኝ : መጣ] 'የት ይሆን የምንሄደው?' ለጥያቄዬ መልሶቻቸው ቁጥብ ፈገግታቸው ብቻ ሆነብኝ ፤ ለማካሄዳቸው መርሆቼ ፍቃድ አገኝ ወደ ነበረው አባቴ ዘንድ ስልክ መታው! ተነሳ....'ሄሎ' ልቅሶ ያሻከረው የሴት ድምፅ ተጆሮዬ አስተጋባ.... [የልቤ : ደርዝ : ተተረከከ፣ጉልበቴ : ተብረከረከ፣ ድምፀቴ : እየተቆራረጠ.. ሄ...ሄ..ሄሎ ባባ የት ሂዶ ነው ስልኩን ያነሳሽው?.....ደግሞ ድምፅሽ ምን ሁኗል?...የጥያቄ መዓት አግተለተልኩባት [የእናቴ ድምፅ ነበር። ወትሮ ከየንግርቷ መሃል የሚያመልጧት ሺ ሳቆች ዛሬ የሉም!....ካለወትሯዋ የጭንቀት ዳመና የዳመነበት ድምፅ እየተብሰለሰለ ከጆሮዬ ሲሰርግ አቅም አጣሁ።] ታኪስ ተኮናትረን አቧራማ መንገዱን እየቀዘፍን አባቴ ወዳለበት ተጣደፍን!....የሚበረው ታኪስ የሚንፏቀቅ መሰለኝ [ለካ : ምንም : የልብን : ያህል : መፍጠን : አይችልም፤ምን : ቢፈጥን : በሀሳብ : መንገድ : ይቀደማል ] ምሽቱ ለአይን ይዟል በጥድፈቴ መሃል ከደረስንበት አንፃር ከፍ ብሎ በሁለት ካስማ ዘንጎች አግድም የተሰቀለ የሆስፒታል ማስተወቂያ አየሁ....ተግቢው ደጃፍ የተቀመጡ ጥበቃዎችን አልፌ ወደ ውስጥ እፈተለክ ጀመር። አባት ጋ ለመድረስ ማላውቃቸው ሰዎች መሃል ተማላውቀው ቦታ 💚💛❤ [የአባትነት : ቅኔው : እንደ : ሰብዓሰገል : የሚመረውን: : ጥድፈት : እጣደፍ : ጀመር ] 💚💛❤ ከህንፃው ገብቼ ኮሪደሩን ስታጠፍ የታማሚ ታሪኳን በእጆቿ መሃል አቅፋ እየመጣች ያለች ዶክተር ጋ ተጋጨን! የታማሚ ታሪኳን የከተበውን ወረቀቶቿ እዚህ እዛ ተበታተኑ...ትቻት አለፍኩ! ካንዱ ክፍል ዘው አልኩ..ብዙ ሰዎች ከመግቢያው በተቀመጠ አግዳሚ ወንበር ተፋፍነው ተቀምጠዋል...አንዳንዱ ይንጎራደዳል... አባቴ ብዙ ላሲትክ ቱቦዎች ተተብትበውበት ከታማሚ አልጋ ተንጋሏል....እናቴም ተጎኑ ባለ ወንበር አንድ እጇን ከአገጯ አኑራ ከአይኖቿ እምባ እየዘረገፈች አይኖቿን ከአይኖቹ ላይ ታንከባልል ነበር!
Biniyam T.
ያያኃት ቅፅበት ወጀብና ማዕበል ነበር ፤ ግትልትል ነፍሴ ሰርክ የምትናጥበት አለም
አየኋት ! [ ተሰራየሁ ] መሰል ፥ ሳያት ሰረነቅሁ ፦ ምራቄ ሰነፈጨኝ - ያኔ ሳይሆን አይቀርም የሀሳብ ግትልትሌ በሰርኔ የወጣሁ ፤ ናላን የምትጎስም ፋቅ - እውኔን የምትሸብቅ ስርቅታ! እሾሆቼን የምትፈነችል ጉጠት ነበረች ! [ አዲዮስ ቢኒያም ! ] ⁿጥቁር በነጭ የተዥጎረጎረ ካናቴራ ለብሳለች ፤ ቀና አልኩ ! ላዕላይ ከናፍሯ ከታችኛው 1በምስስለት እጥፋት ርቋል ! የከናፍሯ ህዳግ እግዜር ባቀለመው ጥቁር መስመር ደምቀዋል ፤ የከናፍሯ ገላ በምጥን ክፋዮች ፍምማ ቀይ ተቀልሟል ። ጠብቀው ያልተከደኑ ከነፍሯ የነጫጭ አስናኗን ንፃሬ ያሳያል ፤ አጠገቧ ሄጄ ልሳለማት ሻትሁ ፤ " ፍችኝ ልላት - እግዜር ይፍታህ ! እንድትለኝ " መናዘዝ ፈለግሁ ! ፤ ነፍሴ የምትመንንባት ገዳም መሰለችኝ ! በምኔትነቷ አለሜን የምትጠፍር የሀሳብ ፈትል ! የትዝታ ክፋክፍት ባሰናሰሉት የናፍቆት ሀዲድ ቀንተሌት መልኳን ወደየሁት ቅፅበት እጥመለመላለሁ ፤ ካወቅኳት እፍታ ወዲህ ኪናዊ ተምኔቴ ናት - ሁለንታ የምስማማባት ብያኔ ! ◉ በምስስለት እጥፋት ( symmetrical fold ) ◉ ፍምማ ቀይ ( blushed red ) ◉ ኪናዊ ተምኔት ( the aesthetic utopia )
Biniyam T.
ለነፍስ የተፃፈ ደብደቤ ፤
Dear soul Am I obsessed with your presence ? Day and night my mind blow to precisely answer who you are. To be honest , I can't . I have heard that at the time when the ship got accident the passengers voluntarily jettisoned there bags , remember the incident in Jonah 1 vs 5 in Bible ? I kindly ask you this, being Obsequious and throw your self then let me define you in your absence . Your Bona fides, Biniyam. እተክዛለሁ በመኖሩ ያልገባኝን የነፍስ ደርዝ ፤ ባለመኖሩ ልረዳ ፤
Biniyam T.
The Exotic Bloom
◉ "እማ" አይኖቹን በአይኖቿ ላይ እያንከባለለ ተጣራት ! _____ በሙሉ አይኑ አያያትም ሲያፈጥባት በአይኖቹ ውስጥ የምትሟሽሽ ይመስለዋል ! ብሌኗ ውስጥ ለመልኩ የተወችለትን ቦታ ለዕጣ ፋንታው የተተወለት ምህዳር ነው። ወንድ አይኖቿን ሲያይ በብሌኗ በኩል የተከዳ ይመስለዋል። ⁴የብሌኗ በራሂ የተቀየጠ ይመስለዋል ፤ _____ ◉" The lust of destiny ! " በረጅሙ እየተነፈሰ ደግም ተጠራት ፤ ◉"እማ ፤ ያችን አበባ አየሻት ? " በጠቋሚ ጣቱ ለፀሐይ ቀንበጧን ዘርግታ የፈካችውን ፅጌረዳ እያሳያት ! ◉"አዎን አባ" እየሳቀችለት መለሰች። _____ ሳቋ ፍም ከናፍሯ መሃል የተወለደ መብረቅ ይመስላል ፤ ሲያስገመግም ነፀብራቁ የሚያሳትብ አይነት ! " በስመአብ ! " ልላት ያምረዋል። የሕይወት ቅዝቃዜውን የምትገፍ ረመጥ ናት። _____ ◉" ይሄ የኔ እና አንቺ አመክኗዊ ዝምድና ይመስለኛል። ቀለም አልባ አባባ ነበርኩ። ከጠቀለልኩት አለም መውጣት የሚፋራ ነፍስ ፤ የነፍስሽን መገለጥ ሀሁ ቆጠርኩ ። ቀይ ደምሽን አዋስሽኝ ፤ ⁵መልክአበባዬን ቀይ ቀለምኩ ፤ የትንፋሽሽ ፍም ጎህ ቀደደልኝ ፤ እሳትነትሽን ሞቅኩ ፤ ከአውድሽ ከታደምኩ ወዲህ የምደብቀው ገመና አልነበረኝም። You are my exotic Bloom ! " አላት ከጉንጩ የሚከነብለውን የናፍቆት እምባ በእጁ አይበሉዋ እየጠረገ ። _____ ⁴ The mutation of genetic pattern in her lens ⁵ I paint red my petals
Biniyam T.
< የንግስሽ እለት ፤ ለቃሌ መያዣዋ ምን ይሆን ? >
ጭጋግማ ውርጭ ባቆረፈደው ፤ ረፍት አልባ ካፊያ በረሰረሰው ውሃልክ ላይ ተቀምጦ ፤ በዛገው የግቢያቸው መቀርቀሪያ ላይ አፍጥጦ ይተክዛል ። __ በእጁ ከያዘው " Tower in the sky " መፅሐፍ መቶኛ ገፅ የገፁን እኩሌታ ለእልባት አጥፏል ። ገፆቹ መሃል ሩብ ወረቀት ላይ የሰፈረ የሴት ምስል ተነድፏል። ወረቀቱ ላይ እየተስለመለመ ፤ ተጣራት ፦ __ < እማ ! > አይኖቹ እምባ አቅርረዋል ፣ እግሮቹ ልደርሱ የለገሙትን ርቀት ልቡ ትታው ለመሄድ ትክ ትክታዋን ታጣድፋለች ። እምባ ሆኖ የፈነገለው ስሜት ከንድፉ ላይ ይንጠባጠባል ። < አየሽ እማ ያራራቀን አንሶት በጎድን አጥንቶች ልቤን እንዴት እንደጠላለፋት ? እህ እማ ዝም አትበይኛ ፤ አኩርፈሽ ነዋ ? . . . እህ እማ ? . . . " ምን አጠፋሁ ? " እሺ በቃ . . . " ምን ልቀጣ ? እህ . . . ል... ል ...ልል...ልሳምሽ ? > _ ከናፍሩን አሹሎ ፤ አይኖቹን በእርግብግቢቱ ከድኖ ቀይ ብዕር ባቀለመችው ከናፍሯ ላይ እንደሰም ቀለጠ። _ አየሽ አይደል እማ ! ፤ አንቺ . . . ታቦት ና ፅላት ፤ መፅሐፍ እና ማህደር ነሽ። በወረብ ፣ በዘፈን ፣ በእልልታና ፀነፀል ነው የማነግስሽ። <የንግስሽ እለት ፤ ለቃሌ መያዣዋ ምን ይሆን ?> ምንም ! ደብረ ቅዱስሽን አልደልልም ። ፅልመቴን ተተግኜ ያለፍኩትን ቅጥር ፣ ፍም ቀናቴን የረሳሁትን ጠለልማ ፤ አልደልልም ! <እኔን ልሳል ?> _ በእጁ በያዘት ብጣሽ ወረቀት ላይ የነደፈችው ምስሏ ረጭ ብላለች። ዝምታዋ ጨነቀው ። የአፍንጫዋን ተረተር በእጆቹ እየደበሰ ። በሰማያዊ ብዕር የከናፈሩን ገላ በሌባ ጣቱ ቀርፃ ከቀኝ ጉንጯ ያተመችውን መሳም እያየ በትዝታ ነጎደ። _ ተፈጥሮን በዙሪያዋ የምታሾር መለኮት መሰለችው። ሲያስባት መወሳሰብን የምትሸሽግ ነፀብራቅ ! ፤ ካወቃት ወዲህ ⁴የሕውስታዎቹ አፀግብሮት ናት ፤ ባለመው የሌት ሕልሞች ፣ በቃዣው ቅዠቶች ልክ ፣ በሰማው ዝማሜ ድምፅ ፤ ከዳሰሰው ልስላሴ ፣ ከፈገገው ጎህ መቅደድ ውስጥ ገዝፎ እሷነቷ ያቃጭልበታል ። _ ⁴the reactions of sensation
Book Review
Biniyam T.
Animal Farm
ኤሪክ ብሌይር ይሰኛል በብዕር ስሙ ደግሞ ጆርጅ ኦርዌል ፤ ካሉት በርካታ መፅሐፍት ውስጥ በዝናው ስለናኘው 'Animal Farm' እንዲህ እንጫወት። _ መፅሐፉ በ1917 የተቀሰቀሰው የሩሲያ አብዮት ሩሲያውያንን ወደምጨቁን አምባገነናዊ መንግስት እንዴት እንደተቀየረ የምታርክ ተምሳሌታዊ ልቦለድ ነው። የታሪኩን ጥንስስ በሀገረ እንግሊዝ ባለ የMr.Jones 'manor Farm' በመተረክ ይጀምራል። Mr.Jones ለእንስሳቱ ግድየለሽ ፣ ሲሻው የሚቀጣ ጨካኝ ፣ ሲሻው የምሸልም ርሁሩህ የእርሻው ጌታ ነበር። ⁵[በእርግጠኛ ባለመሆን መርህ] እንስሳቱን ልያስተዳድር የሚሞክር አይነት የእርሻ ባለቤት! ከእለታት አንድ ቀን 'old major' የተሰኘው አሳማ ከእንስሳቱ ጋ መከረ። ስለምደርስባቸውም በደል 'Beast of England' የተሰኘ የአብዮት ዜማ ደረሰ። መተዳደሪያ ማኒፌስቷቸውንም በእንስሳቱ እኩልነት ፣ በሰው ልጅ ጠላትነት እና እንስሳቱ የተሻለ ሕይወት እንደሚያሻቸው በሚያትት ውቅር መርሆዎች 'Animalism' ብሎ ሰየመ። _ 'manor farm' ሩሲያ ነበረች። ከአብዮቱ በፊት ልክ እንደ Mr.Jones በሚወዥቅ ባህሪ የሚያስተዳድረት ኒኮላስ ሁለተኛ የተሰኘ ንጉሥ የነበራት ሀገር ። ካርል ማክስ የሰራተኛውን መደብ መጨቆን ነፃ የሚያወጣ የኮሚኒዝም ማኒፌስቶን አስተዋወቀ። ሩሲያም ነፃነትን ፍለጋ በተነሳ አብዮት ጋለች። _ ልቦለዱ በ'snowball' እና 'Napoleon' በተሰኙ አሳማዎች አመራር አብዮቱ እንደቀጠለ ይተርካል። snowball ስለእንስሳቱ ሕይወት መሻሻል የምታትር ሀሳባዊ መሪ ሲሆን ፩.አሁናዊ አላማቸውንና የወደፊት ህልማቸውን የሰነደ ባንዲራ አዘጋጀ ። "The flag was green, Snowball explained, to represent the green fields of England, while the hoof and horn signified the future Republic of the Animals which would arise when the human race had been finally overthrown." ፪.ቀለም ጨበጠ የእርሻውንም ስም ANIMAL FARM ብሎ ዳግም ሰየመው "Then Snowball (for it was Snowball who was best at writing) took a brush between the two knuckles of his trotter, painted out MANOR FARM from the top bar of the gate and in its place painted ANIMAL FARM." ፫.የAnimalism ማኒፌስቶን 'በሰባቱ ትዕዛዛት' ፃፈ። THE SEVEN COMMANDMENTS 1. Whatever goes upon two legs is an enemy. 2. Whatever goes upon four legs, or has wings, is a friend. 3. No animal shall wear clothes. 4. No animal shall sleep in a bed. 5. No animal shall drink alcohol. 6. No animal shall kill any other animal. 7. All animals are equal. 'Napoleon' ግን ጨካኝ ፣ መሰሪና ና አምባገነን መሪ ነበረ። ልክ አሜሪካዊው የመድረክ ቧልተኛ የአሜሪካ ፖለቲከኞችን ስወርፍ ⁶"why they call it American dream,to belive them you have to asleep" ያለው የቀልድ አልጎሪ በልኩ የተሰፋለት ገፀባህሪይ ! በእርሻው ውስጥ ጠባቂ ውሾችን በማሰልጠን ግላዊ ሃይሉን አደረጀ፣ 'squealer'ን ለፕሮፓጋንዳው በመጠቀም በእንስሳቱ ዘንድ እምነት አሳደረ ! ከዚያም snowballን ከእርሻው በማሳደድ አባረረው። _ snowball በሩሲያ አብዮት ውስጥ የ "October Revolution" የመራው የፓሊስ ነዳፊው የሊዮን ትሮቶስኪ ተምሳሌት ነበረ ። የሩሲያንም ስም ወደ USSR ቀይሯል። Napoleon ደግሞ ጨካኙን ስታሊን ሲሆን ያሰለጠናቸው ውሾች ደግሞ የስለላውን ዋልታ KGB ተምሳሌት ነበሩ። ልክ እንደ Snowball ትሮቶስኪ በስታሊን ከሀገሩ ሩሲያ ተባሯል። _ Napoleon የአምባገነንነቱን ደርዝ አሰፋ። የታታሪዎቹ እንስሳት እምነት "Napoleon is always right, I must work harder-'Boxer' " ፣ የማያሰላስሉትን በቀላሉ ማሞኘት መቻሉ ፣ በአብዮቱ ውስጥ የራሳቸውን ሕልም የሚያልሙ እንስሳት መኖራቸው (አለ አይደል እንደግራጫ ቃጭሎቹ መዝገቡ ኢምፔሪያሊዝም ይውደም ሲሉ ሰምቶ ልሙጥ ሽሮ ይውደም እንዳለው😂)The stupidest questions of all were asked by Mollie, the white mare. The very first question she asked Snowball was: “Will there still be sugar after the Rebellion? “ እነኚህ ምክንያቶች ለሚቀይራቸው ሕጎች ⁷የቅቡልነትን ሕግን ለማስረፅ እንዲቻለው አቅም ሰጠው ። በእርሻው ላይ ሰባቱ ትዕዛዛት እንዲህ ተለውጠዋል ፤ ◉“No animal shall sleep in a bed” to “No animal shall sleep in a bed with sheets” አልጋ አንጥፈው እየተኘ ፤ ◉"No animal shall drink alcohol" to "No animal shall drink alcohol to excess" በውስኪ ስካር እየተዘፈቀ ፤ ◉"No animal shall kill any other animal" to "No animal shall kill any other animal without cause” ሲሸው እየገደለ በመጨረሻም አሳማዎቹ (የእንስሳት እርሻ ገዢዎች) በእግራቸው ቆመው መሄድ ጀመሩ (ሁለት እግሬዎች የተሻሉ ናቸው ብለውም ሰበኩ) ፤ በስመዲሞክራሲ ናፓሊዮን ብቻውን ያለበትን ምርጫ ተወዳደረ ፣ በሰው ገበታ ውስኪ ተራጬ ፤ ከሰው ማዕድ ጋ አብረው ቆረሱ "ከሰው እስካይለዩ ድረስ ፤ ከሰው ተመሳሰሉ " ልዕለ ሕግም እንዲህ አወጡ፦ “ALL ANIMALS ARE EQUAL BUT SOME ANIMALS ARE MORE EQUAL THAN OTHERS”. _ ሩሲያዊያንም የተጋደሉለት አብዮት ከሰመ ፤ ስታሊንም ካወቋቸው መሪዎች ሁሉ ፍርደገምደልና ጨካኝ ነበር ፤ ከአንደኛው ንግግሩ እንዲህ አለ “Death solves all problems - no man, no problem.” _ BINIYAM T. ⁵principles of uncertainty ⁶Georg Carlin ⁷Rules of recognition
Biniyam T.
በ Harvrd Business Review Press የታተመውን Blue ocean strategy እንይ፦
[ Biniyam T. ] Chapter 1 ደራሲው ገበያን በሁለት ውቅያኖሶች ይመስላል። Red ocean and Blue Ocean. [ Red ocean ] የታወቀ የገበያ ምህዳር ስሆን በዚህ ውቅያኖስ የተዘፈቁ እንዱስትሪዎች defined boundaries እና known competition rules አሏቸው። በተወሰነ የገበያ ፍላጎት (existing Demand) ላይ ይቧደናሉ። የRed ocean መርህን ከ military strategy ጋ ይመስላል [ chief executive officers in headquarters, troops in front lines confronting an opponents over limited given piece of land ] በውስን ገበያ ከመቧጨቅ ሂደት ኃላ አሸናፊዎች ከውቅያኖሱ መሃል ይነግሳሉ ፣ ተሸናፊዎች ከውቅያኖሱ ይሰምጣሉ በጦርነቱ የተረፉ ርዝራዦች ወደውቅያኖሱ ዳር ይገለላሉ። "As market space gets crowded, more products become commodities and the red ocean turns bloody" [ Blue Ocean ] በተቃራኒው ያልታወቀ የገበያ ምህዳር ሲሆን ፣ አንዳንዶቹ አዳዲስ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ሆነው ውቅያኖሱን ሲፈጥሩ ሌሎቹ ደግሞ የred oceanን ወሰን በ " a little of all of them and none of any of them " መርህ በመለጠጥ ይፈጠራሉ። "In Blue Oceans, Competition is irrelevant because the rules of the game are waiting to be set" የ Blue Ocean strategy [ value innovation ] ስሆን ለእሴትና ግኝት እኩል አፅንኦት ይሰጣል። value ያለ innovation የሚሻሻል እሴት ብቻ ይሆንና በገበያ ለመፅናት በቂ ጉልበት አይኖረውም። እንዲሁም innovation ያለ value ቴክኖሎጂ መር ገበያ ብቻ ይሆንና shooting our products beyond what buyers are ready to accept and pay for it. ስለዚህ valueና innovation ተነጣጥለው የተገኙበት ገበያ ሌሎች companies እንድፈለፍሉት እንደተጣለ እንቁላል ይሆናል። value innovation የ Red ocean ገበያ ቅቡልነት ዶግማ የሆነውን Value-Cost Trade-Off [ "Companies can either create greater value to customers at a higher cost or create reasonable value at lower cost."] ያደበዝዛል። በዚህ strategy ምርጫ በ differentiation እና lower cost መሃል ይወድቅ ነበር ፤ ነገር ግን Blue ocean ሁለቱንም simultaneously ይፈጥራል። በዚህም Opportunity maximize and risk minimize የሆነበት የገበያ ምህዳር ይፈጠራል። - Blue Ocean
Biniyam T.
ይሄ መፅሐፍ በBessel van der Kolk የተፃፈ ስሆን
ይሄ መፅሐፍ በBessel van der Kolk የተፃፈ ስሆን [ Trauma ] ና የtraumaው ብልጭታዎች የሰዎችን ሕይወት እንዴት እንደሚያመሰቃቅሉና የመኖርን ትርጉም እንደሚያሳጡኣቸው ያትታል። መፅሐፉ ሕይወቴን ሳያት ታሪኳ የተፋለሰ ነው በሚለው የJessica Stern አባባል እንዲህ ብሎ ይጀምራል ፦ "Some people’s lives seem to flow in a narrative; mine had many stops and starts. That’s what trauma does. It interrupts the plot. . . . It just happens, and then life goes on. No one prepares you for it." ደራሲው በቬትናም ጦርነት ምክንያት ሕይወቱ ስለተመሰቃቀለችበት Tom ስለሚባል ወታደር ሕይወት ያውጠነጥናል። ለ Tom አሰቃቂ የጦርነት ቅዠቶቹ እንዲጠፉለት መድሀኒት ስታዘዝለት በሚያስደንቅ ሁኔታ ክኒኖቹን አልወስድም ይላቸዋል። የTom ምክንያት የነበረው በጦር ሜዳ የተሰዉት ጓደኞቹ በዚህ አለም የሚቀጥሉት በቅዠቱ ውስጥ እንደሆነ ማሰቡ ነበር። ቅዠቱ የሚጠፋ ከሆነ የሞቱትን ጓደኞቹን እየከዳ እንደሆነ ያምናል this emphasizes complex moral dilemmas of traumatic experience. ከዚያ ደራሲው ይጠይቃል ፤ How do horrific experiences cause people to become hopelessly stuck in the past? What happens in people’s minds and brains that keeps them frozen, trapped in a place they desperately wish to escape? Why did this man’s war not come to an end in February 1969 ? Bessel van der Kolk ሰዎች ትላንታቸው ውስጥ በተፈጠረ አስደንጋጭ አጋጣሚ ተተብትበው ዛሬን መኖር ለምን እንደሚያቅታቸው ያትታል ፣ ወደ ፊት እንዳይሄዱ በትላንታቸው ውስጥ ያደነዘዛቸውን trauma ከሳይኮሎጂና neurology አንፃር explore ለማድረግ ይቃትታል ከዚያም ራስን ስለመዋሸት (Self-Deception) ያብራራል ፤ ሰዎች ለራሳቸው የምነግሩት ውሸት የስቃያቸው ዋና ምንጭ ነው። ከ trauma የማገገም መንገድ የምጀምረው ራሳችንን ማታለል ስናቆም እንደሆነ ያስረዳል [ “The greatest sources of our suffering are the lies we tell ourselves.” ] በሼትናሙ ጦርነት ወታደር የነበረው Tom እንዴት የጦር ጓደኞቹ ሕይወት አልባ ማንነት ምስል በአእምሮው እየተደቀነ እንዲሁም ትውስታዎቹ በድምፅ ፣ በሽታ ፣ በምስል ከtraumaው ጋ associate እየደረጉ አስፈሪውን ትላንት እንደሚያስታውሱት እና Tomን ወደ ስሜት ድንዛዜ ( emotional numbness ) እና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ እንድነጠል እንደመሩት ያሳያል። Tom ከቤተሰቦቹ ጋ መቀራረብ ብፈልግም ልቡ አንደደነደነ እና ፍቅር ልሰጣቸው እንዳልቻለ / emotionally distant / እንደሆነ ይነግረናል Tomን የጓደኞቹ መገደል በሰው ልጅ ላይ እምነት እንዳሳጠውና ያን ጊዜ ብዙ ንፁሐንን እንደገደለና ብዙ ሴቶችን እንደደፈረ ያወራል ፤ [ After that it became truly impossible for him to go home again in any meaningful way. How can you face your sweetheart and tell her that you brutally raped a woman, or watch your son take his first step when you are reminded of the child you murdered? ] ይሄም ከጦርነቱ በኃላ ከማህበረሰብ ጋ reintegrated መሆን እንደከበደውና ራሱንም ሌሎችንም በፍፁም ማመን እንደከበደው ይተርካል። [ After you have experienced something so unspeakable, how do you learn to trust yourself or anyone else again? ] ከዚያም ሕመሙን ለማስታገስ Tom ራሱን busy ማድረግ እንደመረጠ ፤ በስራና በአልኮል ውስጥ ከራሱ ለመደበቅ ስጥር ያሰየናል። ነገር ግን ይሄ ጊዜያዊ relief ብቻ እንደሰጠው ያወራል ደራሲው ምናብ ( imagination ) በማገገም ሂደት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነና ሰዎች አዲስ ነገር በምናባቸው ስስሉ ተስፋ እንደምሰርፅባቸው ይነግረናል [ Imagination is absolutely critical to the quality of our lives. Our imagination enables us to leave our routine everyday existence by fantasizing about travel, food, falling in love, or having the last word—all the things that make life interesting. ] በTrauma ለሚሰቀዪ ሰዎች you either belonged to the unit or you were nobody. After trauma the world becomes sharply divided between those who know and those who don’t. ብሎ የመጀመሪያውን ክፍል ሀሳብ ያገባድዳል። 📌 Biniyam T.
Poems



























Contact me
Have you any questions?
I'm at your service
Call me on
+251931392175
Office
5 killo Ethiopia
eftalhom@gmail.com
Website
www.eftalhomtimes.com